18.

ተቀባይነት

አካፍል
  1. እንድታመሰግን ያደረገ ነገር ምንድር ነው?
  2. በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋራ እንዴት ሳለፍክ/ሽ?
  3. እግዝአብሔር ምን እንዲረዳህ ትፈልግሃለህ?
  4. በምያስፈልግህ ነገር ውሰጥ እንዴት ልንረዳህ እንችላለን;
  5. ለእርስበርሳቸችሁ ፀልዩ
ክለሳ
  1. ከባለፈው ስብሰባችን ወዲህ ምን ምን ተለማምደሃል?
  2. የእግዝአብሔርን ለሌሎች ማካፍል ትችላለህ? ከነርሱ ጋር ፀልየሃል?
አንብብ
  1. ንባቡን ድምጽህን ከፍ አርግና ሁለት ግዜ አንብብ
  2. በቡድኑ እርዳታ አንድ ሰው ንባቡን በቃሉ እንዲያነብ አርጉት
  3. የተጨመረ አዲስ ነገር ወይም የጎደለ ነገር አለ?

የሉቃስ ወንጌል 15:11-32

11 እንዲህም አለ፦ አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።

12 ከእነርሱም ታናሹ አባቱን፦ አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።

13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፥ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ።

14 ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፥ እርሱም ይጨነቅ ጀመር።

15 ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ፥ እርሱም እሪያ ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው።

16 እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር፥ የሚሰጠውም አልነበረም።

17 ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።

18 ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥

19 ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።

20 ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።

21 ልጁም፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም አለው።

22 አባቱ ግን ባሪያዎቹን አለ፦ ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ፤

23 የሰባውን ፊሪዳ አምጥታችሁ እረዱት፥ እንብላም ደስም ይበለን፤

24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር።

25 ታላቁ ልጁ በእርሻ ነበረ፤ መጥቶም ወደ ቤት በቀረበ ጊዜ የመሰንቆና የዘፈን ድምፅ ሰማ፤

26 ከብላቴናዎችም አንዱን ጠርቶ፦ ይህ ምንድር ነው? ብሎ ጠየቀ።

27 እርሱም፦ ወንድምህ መጥቶአልና በደኅና ስላገኘው አባትህ የሰባውን ፊሪዳ አረደለት አለው።

28 ተቈጣም ሊገባም አልወደደም፤ አባቱም ወጥቶ ለመነው።

29 እርሱ ግን መልሶ አባቱን፦ እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት እንደ ባሪያ ተገዝቼልሃለሁ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍሁም፤ ለእኔም ከወዳጆቼ ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ ጥቦት ስንኳ አልሰጠኸኝም፤

30 ነገር ግን ገንዘብህን ከጋለሞቶች ጋር በልቶ ይህ ልጅህ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፊሪዳ አረድህለት አለው።

31 እርሱ ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፥ ለእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፤

32 ዳሩ ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም ነበር ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል አለው።


በስፋት አንብብ

አጣራ
  1. ይህ ንባብ ላንተ ምን ጥቅም አለው?
  2. ከዚህ ንባብ የወደድከው ነገር ወይ የረበሸ ነገር አለ?
  3. የህ ንባብ ስለ ሰው እና ስለ እግዝአብሔር ምን ይነግርሃል?
አተግብር
  1. የህን ንባብ መሰረት በማድረግ ታደርግ ዘንድ እግዝአብሔር ካንተ የሚፈልገውን ነገር ጠይቅ፤ ምን ምን ናቸው?
    • መቀየር ያለበት ፀባይ
    • መጠየቅ ያለበት ቃል ክዳን
    • መከተል የሚገባው ምሳሌ
    • መጠበቅ ያለበት ትዕዛዝ
  2. ይህን ለቡድኑ አካፍል