14.

የምንናገራቸው ቃላቶች

አካፍል
  1. እንድታመሰግን ያደረገ ነገር ምንድር ነው?
  2. በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋራ እንዴት ሳለፍክ/ሽ?
  3. እግዝአብሔር ምን እንዲረዳህ ትፈልግሃለህ?
  4. በምያስፈልግህ ነገር ውሰጥ እንዴት ልንረዳህ እንችላለን;
  5. ለእርስበርሳቸችሁ ፀልዩ
ክለሳ
  1. ከባለፈው ስብሰባችን ወዲህ ምን ምን ተለማምደሃል?
  2. የእግዝአብሔርን ለሌሎች ማካፍል ትችላለህ? ከነርሱ ጋር ፀልየሃል?
አንብብ
  1. ንባቡን ድምጽህን ከፍ አርግና ሁለት ግዜ አንብብ
  2. በቡድኑ እርዳታ አንድ ሰው ንባቡን በቃሉ እንዲያነብ አርጉት
  3. የተጨመረ አዲስ ነገር ወይም የጎደለ ነገር አለ?

የማቴዎስ ወንጌል 15:1-20

1 በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና፦

2 ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና አሉት።

3 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ?

4 እግዚአብሔር፦ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ፦ አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና፤

5 እናንተ ግን፦ አባቱን ወይም እናቱን፦ ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥

6 አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም ትላላችሁ፤ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።

7 እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፦

8 ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤

9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።

10 ሕዝቡንም ጠርቶ፦ ስሙ አስተውሉም፤

11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው።

12 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው፦ ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን? አሉት።

13 እርሱ ግን መልሶ፦ የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።

14 ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።

15 ጴጥሮስም መልሶ፦ ምሳሌውን ተርጕምልን አለው።

16 ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን?

17 ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?

18 ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው።

19 ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።

20 ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።


በስፋት አንብብ

አጣራ
  1. ይህ ንባብ ላንተ ምን ጥቅም አለው?
  2. ከዚህ ንባብ የወደድከው ነገር ወይ የረበሸ ነገር አለ?
  3. የህ ንባብ ስለ ሰው እና ስለ እግዝአብሔር ምን ይነግርሃል?
አተግብር
  1. የህን ንባብ መሰረት በማድረግ ታደርግ ዘንድ እግዝአብሔር ካንተ የሚፈልገውን ነገር ጠይቅ፤ ምን ምን ናቸው?
    • መቀየር ያለበት ፀባይ
    • መጠየቅ ያለበት ቃል ክዳን
    • መከተል የሚገባው ምሳሌ
    • መጠበቅ ያለበት ትዕዛዝ
  2. ይህን ለቡድኑ አካፍል