በሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ላይ ለርስ በርሳችን መፀለይ አስፈላጊ ነው::
ቁልፍ ጥያቄ: በጣም አስቸጋሪ በሆነው ሁኔታ ውስጥ የክርስትናን ህይወት እንዴት መኖር እንችላለን?
መግለጫ: በራሳችን ብርታት እግዝአብሔር የምፈልገውን ህይወት መኖር አንችልም:: በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ግን እግዝአብሔር
የምፈልገውን ህይወት ለመኖር ኃይል እናገኛለን::
ማጠቃለያ:
በመንፈስ ቅዱስ በሚሰጠን ኃይል እግዝአብሔር የምፈልገውን ህይወት መኖር እና እርሱን ማስደሰት እንችላለን:: ይህንን ህይወት በራሳችን ኃይል መኖር ብንሞክር ፍሬ አናፈራም: እግዝአብሔር የምፈልገውንም ህይወት መኖር አንችልም:: ስለዚህ ሁል ግዜ በመንፈስ ቅዱስ መደገፍ: መመራትም አለብን::
ከመጀመርያ እንደተማርነው በደምብ ልረዳን የሚችል ምሳሌ መተንፈስ ነው:: ኦክስጂን (ንጽሁ አየር) ወደ ውስጥ: ካርቦንዳዮክሳይድ (የተቃጠለ አየር) ደግሞ ወደ ውጪ እንደምንተነፍስ ሁሉ የመንፈስ ህይወትም እንደዚሁ ነው:: ይህም የመንፈስ መተንፈስ ኃጣታችን ስንናዘዝ (ባለፈው ሳምንት እንደ አየነው) ወደ ውጪ እንተነፍሳለን: በመንፈስ ቅዱስ በሚሰጠን ኃይል በመደገፍ ወደ ውስጥ እንተነፍሳለን:: ሁል ግዜ ይህን ካደረግክ/ሽ እግዝአብሔር ካንተ/ቺ የሚፈልገውን ህይወት መኖር ትችላለህ/ሽ::
በጣም አስፈላጊ ነገር የተማርነውን ስራ ላይ ማዋልነው:: ይህን ለማድረግ ሁላችንም መረዳዳት አለብን:: እነኚ ጥያቄዎች ልረዱን ይችላሉ::
ለማተም ንድፍ አውርድ
firststepswithgod.com/amh/print/7
![]() |
![]() |
![]() |