ክለሳ
- ባለፈው ሳምንት እንድታመሰግን ያደረጉ ምን ምን ነበሩ?
- ያስቸገረህ/ሽ ነገር አለ? እንዴት እንርዳህ/ሽ?
- ለህብረተሰባችን/ለግቢያችን/ለትምህርት ቤታችን ያስፈልጋሉ ብለህ/ሽ የምታስበው/ቢው ነገር አለ?
በሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ላይ ለርስ በርሳችን መፀለይ አስፈላጊ ነው::
- የባለፈው ሳምንት ጥናታችን እንዴት አተገበርከው?
- ታርኩን ለማን አካፈልከው? ምላሻቸውስ ምን ነበር?
ትኩረት
ቁልፍ ጥያቄ: ባለፉት ሳምንታት ስንወያይ የነበረው እንዲገባንና በሱ እንድንኖር ያገዘን ማነው?
መግለጫ: መንፈስ ቅዱስ ልረዳን: እንዲሁም የክርስትናን ህይወት እንድንኖር ልያግዘን ሁል ጊዜ ከኛ ጋር አለ::
ዮሐ 14:15-27
15“ብትወዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።16እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤17እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ አብሮአችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆንታውቁታላችሁ።18ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።19ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ዓለም ከቶ አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። እኔ ሕያው ስለ ሆንሁ እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።20እኔ በአባቴ እንዳለሁ፣ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፣ እኔም ደግሞ በእናንተ እንዳለሁ በዚያ ቀን ትረዳላችሁ።21የሚወደኝ ትእዛዜን ተቀብሎ የሚጠብቅ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
22ከዚያም የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳ፣ “ጌታ ሆይ፣ ታዲያ፣ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው።
23ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ ወደ እርሱ እንመጣለን፤ ከእርሱም ጋር እንኖራለን።24የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
25“አሁን ከእናንተ ጋር እያለሁ ይህን ሁሉ ነግሬአችኋለሁ፤26አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።27ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።
- ከዚህ ክፍል ውስጥ ላንተ/ቺ ትርጉም ያለው ነገር አለ?
- ለመረዳት የከበደህ/ሽ ነገር ነበር?
- የዛሬው ክፍል ስለእግዝአብሔር ምን ይነግረናል? ስለሰዎችስ? በእግዝአብሔር እና በእኛ መካከል ያለው ስላለው ግንኙነትስ?
- ይህ ጽሑፍ እንዴት ከዛህ ጥያቄ ጋር ይመሳሰላል ብለህ ታስባለህ? "ማን ለመረዳት እና የክርስትና ሕይወት መምራት እንድንችል ይረዳናል?"
- ስለዚህ ክፍል ጥያቄ ወይም አስተያየት አለክ/ሽ?
- ዛሬ የተማርነውን ነገር እንዴት ታጠቃልላለህ/ሽ?
- ይህ ክፍል በተጻፈበት ግዜ የነበረ እና አሁን በህብረተሰባችን; በቤተሰባችንና በጓደኞቻችን መካከል እየሆነ ያለው ነገር ተመሳሳይነት አለው?
ማጠቃለያ:
የክርስትናን ህይወት ተረድተን እንድንኖር እግዝአብሔር የምረዳን በመንፈስ ቅዱስ ነው:: መንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ከኛ ጋር በመሆን እግዝአብሔር ያስተማረንን ነገር ያስታውሰናል: የእግዝአብሔር አብሮነትም ያረጋግጥልናል::
ትግበራ (ወደ ስራ መቀየር)
በጣም አስፈላጊ ነገር የተማርነውን ስራ ላይ ማዋልነው:: ይህን ለማድረግ ሁላችንም መረዳዳት አለብን:: እነኚ ጥያቄዎች ልረዱን ይችላሉ::
- ይህ እንዴት ልሆን ይችላል ወይስ በዚህ ለውጥ እንዴት ልትኖር/ሪ ትችላለህ/ሽ? ከእግዝአብሔር ከራስህ እና ከሌሎቹ ጋር እንዴት ትኖራለህ/ሽ?
- ከዚህ ሳምንት ውይዪት በኋላ በህይወትህ ውስጥ ምን ትሰራለህ/ሽ?
- በዝህ ሳምንት የተማርነውን ከማን ጋር ትካፈላለህ? ስለ ምን ትካፈላለህ/ሽ?
በሚመጣው ሳምንት ግዜ በመስጠት እነኚን ተጨማሪ ክፍሎች ተመልከት::
ገላትያ 5:16-26
16እንግዲህ በመንፈስ ኑሩ እላለሁ፤ የሥጋንም ምኞት አትፈጽሙም። 17ሥጋ መንፈስ የማይፈልገውን፣ መንፈስም ሥጋ የማይፈልገውን ይመኛልና፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ስለሚጋጩ፣ የምትፈልጉትን አታደርጉም። 18በመንፈስ ብትመሩ ግን፣ ከሕግ በታች አይደላችሁም።
19የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኵሰት፣ መዳራት፣ 20ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቊጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ አድመኝነት፤ 21ምቀኝነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
22የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ 23ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንደነዚህ ያሉትንም የሚከለክል ሕግ የለም። 24የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል። 25በመንፈስ የምንኖር ከሆን፣ በመንፈስ እንመላለስ። 26እርስ በርሳችን እየተጎነታተልንና እየተቀናናን በከንቱ ውዳሴ አንመካ።
ኤፌሶን 5:15-18
15እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ። 16ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። 17ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ። 18በመንፈስ ተሞሉ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ብክነት ነውና።
1 ቆሮንቶስ 2:9-3:3
9ይሁን እንጂ፣ እንደ ተጻፈው፣
“ዐይን ያላየውን፣
ጆሮ ያልሰማውን፣
የሰውም ልብ ያላሰበውን፣
እግዚአብሔር ለሚወዱት አዘጋጅቶአል፤”
10እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል።
መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። 11በውስጡ ካለው ከራሱ መንፈስ በስተቀር ከሰው መካከል የአንድን ሰው ሐሳብ የሚያውቅ ማን አለ? እንደዚሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በስተቀር፣ የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚያውቅ ማንም የለም። 12ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤ ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው። 13እኛ የምንናገረው ይህን ነው፤ ከሰው ጥበብ በተማር ነው ቃል ሳይሆን፣ ከመንፈስ በተማር ነው ቃል እንናገራለን፤ መንፈሳዊ እውነትንም የምንገልጸው በመንፈሳዊ ቃል ነው።14መንፈሳዊ ያልሆነ ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የሆነውን ነገር ሊቀበል አይችልም፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ነገር ለእርሱ ሞኝነት ነው፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ፣ ሊረዳው አይችልም። 15መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉንም ነገር ይመረምራል፤ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።
16“ያስተምረው ዘንድ፣
የጌታን ልብ ማን ዐወቀው?”
እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
1ወንድሞች ሆይ፤ በክርስቶስ ገና ሕፃናት እንደመሆናችሁ፣ እንደ ሥጋውያን እንጂ እንደ መንፈሳውያን ልናገራችሁ አልቻልሁም። 2ገና ስላልጠነከራችሁ ወተት እንጂ ጠንካራ ምግብ አልመገብኋችሁም፤ አሁንም ቢሆን ገና ናችሁ። 3አሁንም ሥጋውያን ናችሁ፤ በመካከላችሁ ቅናትና ክርክር አለ፤ ታዲያ፣ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? ተግባራችሁስ እንደ ማንኛውም ሰው ተግባር መሆኑ አይደለምን?
ለማተም ንድፍ አውርድ
firststepswithgod.com/amh/print/6