5.

በመንፈስ ማደግ

ክለሳ
  1. ባለፈው ሳምንት እንድታመሰግን ያደረጉ ምን ምን ነበሩ?
  2. ያስቸገረህ/ሽ ነገር አለ? እንዴት እንርዳህ/ሽ?
  3. ለህብረተሰባችን/ለግቢያችን/ለትምህርት ቤታችን ያስፈልጋሉ ብለህ/ሽ የምታስበው/ቢው ነገር አለ?

በሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ላይ ለርስ በርሳችን መፀለይ አስፈላጊ ነው::

  1. የባለፈው ሳምንት ጥናታችን እንዴት አተገበርከው?
  2. ታርኩን ለማን አካፈልከው? ምላሻቸውስ ምን ነበር?
ትኩረት

ቁልፍ ጥያቄ: ከኢየሱስ ጋር ባለን ግንኙነት ማደግን እንዴት ማስቀጠል እንችላለን?

መግለጫ: በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ መነጋገር ወሳኝ ነው:: እግዝአብሔር ከኛ ጋር ማውራት ይፈልጋል: እኛም ከርሱ ጋር ማውራት አለብን::

የሐዋ 2:42-47

42እነርሱም በሐዋርያት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውንም በመቍረስና በጸሎት ይተጉ ነበር። 43በሐዋርያት እጅ ብዙ ድንቅና ታምራት ይደረግ ስለ ነበር፣ ሰው ሁሉ ፍርሀት አደረበት። 44ያመኑት ሁሉ በአንድነት ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ የጋራ አደረጉ። 45ሀብታቸውንና ንብረታቸውንም እየሸጡ ለእያንዳንዱ ሰው የሚያስፈልገውን ያህል ይሰጡት ነበር። 46በየዕለቱ በቤተ መቅደስ በአንድነት እየተገናኙ፣ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በቀና ልብ ይመገቡ ነበር፤ 47እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው፤ ጌታም የሚድኑትን በቍጥራቸው ላይ ዕለት በዕለት ይጨምር ነበር።



  1. ከዚህ ክፍል ውስጥ ላንተ/ቺ ትርጉም ያለው ነገር አለ?
  2. ለመረዳት የከበደህ/ሽ ነገር ነበር?
  3. የዛሬው ክፍል ስለእግዝአብሔር ምን ይነግረናል? ስለሰዎችስ? በእግዝአብሔር እና በእኛ መካከል ያለው ስላለው ግንኙነትስ?
  4. ይህ ጽሑፍ እንዴት ከዛህ ጥያቄ ጋር ይመሳሰላል ብለህ ታስባለህ? "እንዴት ከኢየሱስ ጋር ግንኙነት እያደገ መቀጠል ለምንድን ነው?"
  5. ስለዚህ ክፍል ጥያቄ ወይም አስተያየት አለክ/ሽ?
  6. ዛሬ የተማርነውን ነገር እንዴት ታጠቃልላለህ/ሽ?
  7. ይህ ክፍል በተጻፈበት ግዜ የነበረ እና አሁን በህብረተሰባችን; በቤተሰባችንና በጓደኞቻችን መካከል እየሆነ ያለው ነገር ተመሳሳይነት አለው?

ማጠቃለያ:

በፀሎት ከእግዝአብሔር ጋር በመነጋገር: በመጽሓፍ ቅዱስ እና ከክርስትያኖች ጋር በመገናኘት እርሱን በመስማት ከኢየሱስ ጋር ባለን ግንኙነት ማደግ እንችላለን:: እንዲህ እርሱን ማወቅ እንችላለን::

ትግበራ (ወደ ስራ መቀየር)

በጣም አስፈላጊ ነገር የተማርነውን ስራ ላይ ማዋልነው:: ይህን ለማድረግ ሁላችንም መረዳዳት አለብን:: እነኚ ጥያቄዎች ልረዱን ይችላሉ::

  1. ይህ እንዴት ልሆን ይችላል ወይስ በዚህ ለውጥ እንዴት ልትኖር/ሪ ትችላለህ/ሽ? ከእግዝአብሔር ከራስህ እና ከሌሎቹ ጋር እንዴት ትኖራለህ/ሽ?
  2. ከዚህ ሳምንት ውይዪት በኋላ በህይወትህ ውስጥ ምን ትሰራለህ/ሽ?
  3. በዝህ ሳምንት የተማርነውን ከማን ጋር ትካፈላለህ? ስለ ምን ትካፈላለህ/ሽ?


ለማተም ንድፍ አውርድ
firststepswithgod.com/amh/print/5