3.

የእግዝአብሔር ፍቅርና ምህረት መለማመድ

ክለሳ
  1. ባለፈው ሳምንት እንድታመሰግን ያደረጉ ምን ምን ነበሩ?
  2. ያስቸገረህ/ሽ ነገር አለ? እንዴት እንርዳህ/ሽ?
  3. ለህብረተሰባችን/ለግቢያችን/ለትምህርት ቤታችን ያስፈልጋሉ ብለህ/ሽ የምታስበው/ቢው ነገር አለ?

በሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ላይ ለርስ በርሳችን መፀለይ አስፈላጊ ነው::

  1. የባለፈው ሳምንት ጥናታችን እንዴት አተገበርከው?
  2. ታርኩን ለማን አካፈልከው? ምላሻቸውስ ምን ነበር?
ትኩረት

ቁልፍ ጥያቄ: ከእግዝአብሔር ጋር ጥሩ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት እንዴት መለማመድ እንችላለን?

መግለጫ: ኃጥአታችን ከእግዝአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነታችን ይጎዳል: ከርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ግን ፀንቶ ይኖራል::

ሉቃ 15:11-24

11ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።12ከእነርሱም ታናሹ ልጅ አባቱን፣ ‘አባቴ ሆይ፤ ከሀብትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው፤ አባትየውም ሀብቱን ለልጆቹ አካፈላቸው።
13“ብዙም ቀን ሳይቈይ፣ ታናሹ ልጅ ድርሻውን ሁሉ ጠቅልሎ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ በዚያም በማጋጣነት ንብረቱን አባከነ።14እርሱም ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ በዚያ አገር ሁሉ ጽኑ ራብ ሆነ፤ ይቸገርም ጀመር።15ስለዚህ ከዚያ አገር ነዋሪዎች አንዱን ተጠጋ፤ ሰውየውም ዐሣማ እንዲቀልብለት ወደ ዕርሻው ላከው።16ዐሣማዎቹ የሚመገቡትን ዐሠር እንኳ ለመብላት ይመኝ ነበር፤ ነገር ግን ይህን እንኳ የሚሰጠው ሰው አልነበረም።
17“ልብ በገዛ ጊዜ ግን እንዲህ አለ፤ ‘ስንቱ የአባቴ ሠራተኛ ምግብ ተርፎታል፤ እኔ ግን እዚህ በራብ ልሞት ተቃርቤአለሁ18ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና፣ እንዲህ ልበለው፤ “አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤19ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም፤ ከተቀጠሩት አገልጋዮችህ እንደ አንዱ ቍጠረኝ።’20ስለዚህም ተነሥቶ ወደ አባቱ ሄደ።
“ነገር ግን፣ እርሱ ገና ሩቅ ሳለ፣ አባቱ አይቶት ራራለት፤ ወደ እርሱም እየሮጠ ሄዶ ዐቅፎ ሳመው።
21“ልጁም፣ ‘አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው።
22“አባቱ ግን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤23የሰባውንም ፍሪዳ አምጡና ዕረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት፤24ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር፤ ተገኝቶአል።” ከዚያም ይደሰቱ ጀመር።



  1. ከዚህ ክፍል ውስጥ ላንተ/ቺ ትርጉም ያለው ነገር አለ?
  2. ለመረዳት የከበደህ/ሽ ነገር ነበር?
  3. የዛሬው ክፍል ስለእግዝአብሔር ምን ይነግረናል? ስለሰዎችስ? በእግዝአብሔር እና በእኛ መካከል ያለው ስላለው ግንኙነትስ?
  4. ይህ ጽሑፍ እንዴት ከዛህ ጥያቄ ጋር ይመሳሰላል ብለህ ታስባለህ? "እንዴት ሁልጊዜ ከአምላክ ጋር የቀረበ ዝምድና ማግኘት ትችላለህ?"

ማጠቃለያ:

1 ዮሐ 1:9

9ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃ ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።



ኃጥአታችን መናዘዝ የሰራነውን መጥፎ ነገር ለእግዝአብሔር ነግረን ይቅርታ (ምህረት) መለመን ነው:: እግዝአብሔር ደግሞ ኃጥአታችን ለርሱ ከነገርን ይቅር እንደሚለን ቃል ገብቶልናል::

ኃጥአታችን ትተን ወደ እግዝአብሔር በመመለስ ኢየሱስ ለኛ እንድሞት በሰጠን በዚያ ፍቅርና ምህረት መለማመድ እንችላለን:: ክፉ የመባል: የመነቀፍ እና የመቀጣት ፋንታ ከእግዝአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ይታደሳል::

ትግበራ (ወደ ስራ መቀየር)

በጣም አስፈላጊ ነገር የተማርነውን ስራ ላይ ማዋልነው:: ይህን ለማድረግ ሁላችንም መረዳዳት አለብን:: እነኚ ጥያቄዎች ልረዱን ይችላሉ::

  1. ይህ እንዴት ልሆን ይችላል ወይስ በዚህ ለውጥ እንዴት ልትኖር/ሪ ትችላለህ/ሽ? ከእግዝአብሔር ከራስህ እና ከሌሎቹ ጋር እንዴት ትኖራለህ/ሽ?
  2. ከዚህ ሳምንት ውይዪት በኋላ በህይወትህ ውስጥ ምን ትሰራለህ/ሽ?
  3. በዝህ ሳምንት የተማርነውን ከማን ጋር ትካፈላለህ? ስለ ምን ትካፈላለህ/ሽ?

ለማተም ንድፍ አውርድ
firststepswithgod.com/amh/print/3