2.

ማረጋገጫ

ክለሳ
  1. ባለፈው ሳምንት እንድታመሰግን ያደረጉ ምን ምን ነበሩ?
  2. ያስቸገረህ/ሽ ነገር አለ? እንዴት እንርዳህ/ሽ?
  3. ለህብረተሰባችን/ለግቢያችን/ለትምህርት ቤታችን ያስፈልጋሉ ብለህ/ሽ የምታስበው/ቢው ነገር አለ?

በሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ላይ ለርስ በርሳችን መፀለይ አስፈላጊ ነው::

  1. የባለፈው ሳምንት ጥናታችን እንዴት አተገበርከው?
  2. ታርኩን ለማን አካፈልከው? ምላሻቸውስ ምን ነበር?
ትኩረት

ቁልፍ ጥያቄ:  ኢየሱስን የተቀበለ ሰው ከእግዝአብሔር ጋር ለዘላለም እንደሚኖር እንዴት ማወቅ ይችላል?

መግለጫ:  ከእግዝአብሔር ጋር ግንኙነት እንዳለህ/ሽ ማወቅ ትችላለህ/ሽ::

ዮሐ 10:7-30

7 ስለዚህ ኢየሱስ ዳግም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ። 8 ከእኔ በፊት የመጡት ሁሉ ሌቦችና ቀማኞች ነበሩ፤ በጎቹ ግን አልሰሟቸውም። 9 በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል ፤ ይገባል፤ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል። 10 ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።”
11 “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል፤ 12 ተቀጣሪው እረኛ ግን በጎቹ የእርሱ ስላልሆኑ፣ ተኵላ ሲመጣ ጥሎአቸው ይሸሻል፤ ተኵላውም በጎቹን ይነጥቃል፤ ይበትናቸዋልም። 13 የሚሸሸውም ተቀጣሪ ስለ ሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው።
14 “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን ዐውቃለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፤ 15 ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው ነው። ሕይወቴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ። 16 ከዚህ ጒረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት አለብኝ። እነርሱም ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ። 17 መልሼ ለማንሣት ሕይወቴን አሳልፌ ስለምሰጥ አባቴ ይወደኛል። 18 ሕይወቴን በራሴ ፈቃድ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ አሳልፌ ለመስጠትም ሆነ ለማንሣት ሥልጣን አለኝ፤ ይህን ትእዛዝ የተቀበልሁትም ከአባቴ ነው።”
19 ከዚህም ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ተፈጠረ። 20 ብዙዎቹም፣ “ጋኔን ያደረበት እብድ ነው፤ ለምን ትሰሙ ታለችሁ?” አሉ።
21 ሌሎች ግን፣ “ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው ንግግር አይደለም፤ ጋኔን የዐይነ ስውርን ዐይን መክፈት ይችላልን?” አሉ።
22 በኢየሩሳሌምም የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል  ሆነ፤ ጊዜውም ክረምት ነበረ፤ 23 ኢየሱስም በቤተ መቅደስ ግቢ፣ በሰሎሞን መመላለሻ ያልፍ ነበር፤ 24 አይሁድም ከበውት፣ “እስከ መቼ ልባችንን አንጠልጥለህ ታቈየናለህ? አንተ ክርስቶስ  ከሆንህ በግልጽ ንገረን” አሉት።
25 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሳላቸው፤ “እኔ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ታምራትም ስለ እኔ ይናገራሉ፤ 26 እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም፤ 27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፤ 28 እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም። 29 እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል ፤ ከአባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም። 30 እኔና አብ አንድ ነን።”



  1. ከዚህ ክፍል ውስጥ ላንተ/ቺ ትርጉም ያለው ነገር አለ?
  2. ለመረዳት የከበደህ/ሽ ነገር ነበር?
  3. የዛሬው ክፍል ስለእግዝአብሔር ምን ይነግረናል? ስለሰዎችስ? በእግዝአብሔር እና በእኛ መካከል ያለው ስላለው ግንኙነትስ?
  4. ይህ ጽሑፍ እንዴት ከዛህ ጥያቄ ጋር ይመሳሰላል ብለህ ታስባለህ?  "እንዴት የተቀበለ አንድ ሰው ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ይኖራሉ ብለን በእርግጠኝነት ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?"
  5. ስለዚህ ክፍል ጥያቄ ወይም አስተያየት አለክ/ሽ?
  6. ዛሬ የተማርነውን ነገር እንዴት ታጠቃልላለህ/ሽ?
  7. ይህ ክፍል በተጻፈበት ግዜ የነበረ እና አሁን በህብረተሰባችን; በቤተሰባችንና በጓደኞቻችን መካከል እየሆነ ያለው ነገር ተመሳሳይነት አለው?

ማጠቃለያ:

1 ዮሐ 5:11-13

11 ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። 12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።  13 በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ እናንተ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ፤



መልካም እረኛ የሆነ ኢየሱስ ስለ ኃጥአታችን ነፍሱን በመስቀል ላይ መስዋዕት አደረገ:: ኢየሱስን ጌታችን አና አዳኛችን ስናደርግ እርሱን የሚከተሉ በጎቹ እንሆናለን::እርሱ ማንም ልወስድብን የማይችል የዘላለም ህይወት እንዳለን እንድናውቅ ይፈልጋል:: ኢየሱስን በህይወትህ/ሽ ውስጥ እንደ ተቀበልክ/ሽ ታቀዋለህ/ሽ? የዘላለም ህይወት እንዳለህ በእችግጠኝነት ታቀዋለህ/ሽ?

ትግበራ (ወደ ስራ መቀየር)

በጣም አስፈላጊ ነገር የተማርነውን ስራ ላይ ማዋልነው:: ይህን ለማድረግ ሁላችንም መረዳዳት አለብን:: እነኚ ጥያቄዎች ልረዱን ይችላሉ::

  1. ይህ እንዴት ልሆን ይችላል ወይስ በዚህ ለውጥ እንዴት ልትኖር/ሪ ትችላለህ/ሽ? ከእግዝአብሔር ከራስህ እና ከሌሎቹ ጋር እንዴት ትኖራለህ/ሽ?
  2. ከዚህ ሳምንት ውይዪት በኋላ በህይወትህ ውስጥ ምን ትሰራለህ/ሽ?
  3. በዝህ ሳምንት የተማርነውን ከማን ጋር ትካፈላለህ? ስለ ምን ትካፈላለህ/ሽ?

ለማተም ንድፍ አውርድ
firststepswithgod.com/amh/print/2