እግዝአብሔርን ማወቅ

 

ማንኛውም ነገር ደንብና ስርዓት አለው፡፡ ሰው የሠራቸው ነገሮች ሰው ሰራሽ ስርዓት እንዳላቸው ሁሉ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ነገሮች ደግም የተፈጥሮ ሕግጋት አሏቸው፡፡

1. እግዚአብሔር ይወድሃል ስለዚህም ለሕይወትህ አስደናቂ ዕቅድ አዘጋጅቶልሃል፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡”(ዮሐ 3፡16)

የእግዚአብሔር ዕቅድ

ክርስቶስ እንዲህ አለ፡- “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ፡፡” (ዮሐ 10፡10)

ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ይህንን መሉና አርኪ ሕይወት አልተለማመዱም ምክንያቱም ...

2. ሰው ኃጢአተኛ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይቷል፡፡ ስለዚህም የእግዚአብሔርን ፍቅርና ዕቅድ ማወቅና በሕይወቱ መለማመድ አይችልም፡፡

ሰው ኃጥአተኛ ነው

“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡”(ሮሜ 3፡23)

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ከእርሱ ጋር የቀረበ ግንኙነት በመመስረት በደስታ እንዲኖር ነበር፡፡ነገር ግን ሰው በራሱ መንገድ ለመጓዝ በመምረጡ ግንኙነታቸው ተቋረጠ፡፡ በራሳችን መንገድ ስንጓዝ ለእግዚአብሔር የማንታዘዝና ለርሱም ግድ የሌለን እንሆናለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አይነቱን አስተሳሰብ ነው ኃጢአት ብሎ የሚጠራው፡፡

ሰው ከእግዚአብሔር ተለይቷል

“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና” (ሮሜ 6፡23) ይህም ሞት በመንፈስ ከእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው፡፡

ይህ ስዕል የሚያሳው እግዚአብሔር ቅዱስ ሰው ደግሞ ኃጢአተኛ በመሆኑ በመካከላቸው ትልቅ መለያየት መኖሩን ነው፡፡ ቀስቶቹ የሚያመለክቱት ሰው በራሱ መንገድ ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ እንዴት እንደሚጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የሃይማኖት ስርአቶችን በመፈፀም፣ ቤተክርስትያን ሳያቋርጥ በመመላለስ፣ መልካምን ስራ በመስራት፣ ሰውን ባለመጉዳት፣ወ.ዘ.ተ. ነገር ግን ሰውን ጥረቱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበው አልቻለም፡፡

ሦስተኛው ህግ ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚደርስበትን ብቸኛ ሕግ ያሳየናል.....

3. ሰው ወደ እግዚአብሔር ሊደርስ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለዚህም ሰው በእርሱ በኩል የእግዚአብሔርን ፍቅርና ዕቅድ ሊያውቅና ሊለማመድ ይችላል፡፡

እርሱ ስለ እኛ ሞቷል፡፡

‹‹ነገር ግን ገና ኃጢያተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል፡፡›› (ሮሜ. 5፡8)

ከሞት ተነስቷል

‹‹…ክርስቶስ ስለ ኃጢያታችን ሞተ ተቀበረም መጽሐፍ እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፣ …›› (1ኛ ቆሮ. 15፡3-5)

እርሱ ብቸኛ መንገድ ነው

ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም›› (ዩሐ› 14፡6)

ይህ ስዕል የሚያሳየው እኛን ወደ ራሱ ሊመልሰን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ይህንንም ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በመስቀል ላይ ስለእኛ እንዲሞት በመላክ ፈጽሞታል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሁላችንም በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር መድረስ እንችላለን፡፡

ነገር ግን እነዚህን ሦስት ሕጎች ብቻ ማወቅ በቂ አይደለም......

4. እያንዳንዳችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችንና እንደ ጌታችን ልንቀበለው ይገባናል፡፡ ከዚያም የእግዚአብሔርን ፍቅርና ዕቅድ በሕይወታችን ልናውቅና ልንለማመድ እንችላለን፡፡

ክርስቶስን ልንቀበለው ይገባናል

‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው›› (ዩሐ.1፡12)

ክርስቶስን በእምነት ልንቀበለው ይገባልहै

‹‹ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም›› (ኤፌ. 2፡8-9) 

ክርስቶስን ስንቀበል ዳግመኛ ልደትን እንለማመዳለን (ዩሐ.3:1-8 ን አንብቡ)

ክርስቶስን በግል በመጋበዝ ልንቀበለው ይገባል

ክርስቶስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል›› (ራዕ. 3፡20)

ክርስቶስን መቀበል የሚከተሉትን ያጠቃልላል...

እነዚህ ሁለት ክቦች ሁለት አይነት ሕይወት ይወክላሉ

በእኔነት ቁጥጥር ስር ያለ ሕይወት

በክርስቶስ ቁጥጥር ያለ ሕይወት

እ - ይህ ሰው የራሱን ሕይወት የሚቆጣጠረው ራሱ ነው

† - ክርስቶስ ከሕይወቱ ውጪ ነው

• - ሕይወቱን በተለያየ አቅጣጫ የሚመራው ራሱ ነው ውጤቱም ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ማጣት ነው፡፡

† - በዚህ ሰው ህይወት እና ዙፋን ላይ ክርስቶስ አለ

እ - የዚህ ሰው ሕይወት ተቆጣጣሪ ክርስቶስ ነው

• - በማንኛውም አቅጣጫ ክርስቶስ ሕይወቱን እንዲቆጣጠርለት ፈቅዷል ውጤቱም ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም መፍጠር ነው፡፡

የትኛው ክብ ሕይወትህን ይወክላል?

ሕይወትህ የትኛውን ክብ እንዲመስል ትፈልጋለህ?

የሚቀጥለው ክርስቶስን እንዴት መቀበል እንደምትችል ያብራራል...

አሁኑኑ ክርስቶስን በእምነት ልትቀበል ትችላለህ

(ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር ማውራት ነው)

እግዚአብሔር ልብህን ስለሚያውቅ ልታታልለው አትችልም፡፡

እንዲህ ልትፀልይ ትችላለህ


‹‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ አንተን በግሌ ለማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ ስለ ኃጢያቴ በመስቀል ላይ ስለሞትክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሁን ልቤን ከፍቼ አዳኜና ጌታዬ አድርጌ እቀበልሃለሁ፡፡ ኃጢያቴን ሁሉ ይቅር ስላልከኝና የዘላለም ሕይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፤፤ በሕይወቴ ዙፋን ላይ ሆነህ ግዛኝ አንተ የምትፈልገው ዓይነት ሰው አድርገኝ፡፡ አሜን!››

ይህን ፀሎት ልትፀልይ ትወዳለህን?

ፈቃደኛ ሆነህ አሁኑኑ ብትፀልይ በሰጠው ተስፋ መሰረት ክርስቶስ ወደ ሕይወትህ ይመጣል፡፡