10.

አዲስ ህይወት

አካፍል
  1. በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋራ እንዴት ሳለፍክ/ሽ?
  2. እንድታመሰግን ያደረገ ነገር ምንድር ነው?
  3. እግዝአብሔር ምን እንዲረዳህ ትፈልግሃለህ?
  4. በምያስፈልግህ ነገር ውሰጥ እንዴት ልንረዳህ እንችላለን;
  5. ለእርስበርሳቸችሁ ፀልዩ
ክለሳ
  1. ከባለፈው ስብሰባችን ወዲህ ምን ምን ተለማምደሃል?
  2. እያንከባከብካቸው ያሉተ ሰዎች እንዴት ናቸው? በጣም የሚጠቅማቸው ነገር ምነድር ነው?
  3. የእግዝአብሔርን ለሌሎች ማካፍል ትችላለህ? ከነርሱ ጋር ፀልየሃል?
  4. ለነዚያ ሰዎች ፀልይ
አንብብ
  1. ንባቡን ድምጽህን ከፍ አርግና ሁለት ግዜ አንብብ
  2. በቡድኑ እርዳታ አንድ ሰው ንባቡን በቃሉ እንዲያነብ አርጉት
  3. የተጨመረ አዲስ ነገር ወይም የጎደለ ነገር አለ?

ወደ ሮሜ ሰዎች 6:3-14

3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?

4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።

5 ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤

6 ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።

9 ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና።

10 መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል።

11 እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።

12 እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤

13 ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

14 ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።


በስፋት አንብብ

አጣራ
  1. ይህ ንባብ ላንተ ምን ጥቅም አለው?
  2. ከዚህ ንባብ የወደድከው ነገር ወይ የረበሸ ነገር አለ?
  3. የህ ንባብ ስለ ሰው እና ስለ እግዝአብሔር ምን ይነግርሃል?
አተግብር
  1. የህን ንባብ መሰረት በማድረግ ታደርግ ዘንድ እግዝአብሔር ካንተ የሚፈልገውን ነገር ጠይቅ፤ ምን ምን ናቸው?
    • መቀየር ያለበት ፀባይ
    • መጠየቅ ያለበት ቃል ክዳን
    • መከተል የሚገባው ምሳሌ
    • መጠበቅ ያለበት ትዕዛዝ
  2. ይህን ለቡድኑ አካፍል
ማስታወሻ

የምከተለው የመጽሓፍ ቅዱስ ጥናት ስለ ጥምቀት ነው፡፡ በዚህ ግዜ፣ “ጥምቀት” የምለው ቃል በብዙ ቦታ ተጠቅመው ስለ ሆነ በደምብ ማብራራት አስፈላጊ ነው፡፡

በዙ ሰዎች “ጥምቀት” የምለወን ቃል በብዙ ትርጉም ይረዳሉ፡፡ አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፡

  • • የእግዝአብሔርን በረከት ለልጆች መጠየቅ
  • • ከኃጥአት ለመታጠብ
  • • የእምነትን አቋም ለመግለጽ
  • • ለልጅ ስም ለመሰየም
  • • መንፈሳዊ አባት / እናት ለመሰየም የሚደረግ በዓል

እነኚህ የ “ጥምቀት” አይነቶች ሁሉ ትክክል የምሆኑበት የየራሳቸው ቦታ አላቸው፤ በዚህ ቦታ እያልን ያለነው “ጥምቀት” ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ በዛሬው የመጽሓፍ ቅዱስ ንባባችን ውስጥ “ጥምቀት” ማለት “መለየት” ወይም “መካፈል / መሳተፍ” ማለት ነው፡፡

ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ነበር የተጠመቀው፡፡ደቀ መዛሙርቱም ከመልዕክቱ ጋር መለየት የፈለጉትን ወጣቶችን አጠመቁ፡፡ ጥምቀት እራስን ከማርጠብ ይበልጣል፡፡ በዚህ ትምህርት መጽሓፍ ቅዱስ ስለ “ጥምቀት” አስፈላግነትን የምነግረንን እናያለን፡፡