9.

ጠቢብ ወይ ሞኝ

አካፍል
  1. በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋራ እንዴት ሳለፍክ/ሽ?
  2. እንድታመሰግን ያደረገ ነገር ምንድር ነው?
  3. እግዝአብሔር ምን እንዲረዳህ ትፈልግሃለህ?
  4. በምያስፈልግህ ነገር ውሰጥ እንዴት ልንረዳህ እንችላለን;
  5. ለእርስበርሳቸችሁ ፀልዩ
ክለሳ
  1. ከባለፈው ስብሰባችን ወዲህ ምን ምን ተለማምደሃል?
  2. እያንከባከብካቸው ያሉተ ሰዎች እንዴት ናቸው? በጣም የሚጠቅማቸው ነገር ምነድር ነው?
  3. የእግዝአብሔርን ለሌሎች ማካፍል ትችላለህ? ከነርሱ ጋር ፀልየሃል?
  4. ለነዚያ ሰዎች ፀልይ
አንብብ
  1. ንባቡን ድምጽህን ከፍ አርግና ሁለት ግዜ አንብብ
  2. በቡድኑ እርዳታ አንድ ሰው ንባቡን በቃሉ እንዲያነብ አርጉት
  3. የተጨመረ አዲስ ነገር ወይም የጎደለ ነገር አለ?

የማቴዎስ ወንጌል 7:24-29

24 ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።

25 ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።

26 ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።

27 ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።

28 ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን

29 እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና።


በስፋት አንብብ

>የያዕቆብ መልእክት 1:22

22 ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።


በስፋት አንብብ

አጣራ
  1. ይህ ንባብ ላንተ ምን ጥቅም አለው?
  2. ከዚህ ንባብ የወደድከው ነገር ወይ የረበሸ ነገር አለ?
  3. የህ ንባብ ስለ ሰው እና ስለ እግዝአብሔር ምን ይነግርሃል?
አተግብር
  1. የህን ንባብ መሰረት በማድረግ ታደርግ ዘንድ እግዝአብሔር ካንተ የሚፈልገውን ነገር ጠይቅ፤ ምን ምን ናቸው?
    • መቀየር ያለበት ፀባይ
    • መጠየቅ ያለበት ቃል ክዳን
    • መከተል የሚገባው ምሳሌ
    • መጠበቅ ያለበት ትዕዛዝ
  2. ይህን ለቡድኑ አካፍል
ማስታወሻ

በማቴዎስ 7:24 ላይ ኢየሱስ መጽሓፍ ቅዱስ ስናነብ እንዴት መተግበር እንዳለብን መሰረታዊ አካሄድ በምሳሌ አስቀምጦልናል፡፡ያዕቆብም በመልዕክቱ እንዲ ሲል አጠቃለውታል፡ “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ፡፡” (ያዕቆብ 1፡22)