የማቴዎስ ወንጌል 6:9-15
9 እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥
10 ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
11 የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤
12 እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤
13 ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።
14 ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤
15 ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።
ምንም እንኳን የኢየሱስ ሞት እና ትንሳዔ ለሁሉም ሰው ኃጥአት ዋጋ የተከፈለ ብሆንም፣ ኃጥአት ባንዴ ወይ በቅዝበት ይቅር ይባላል ማለት አይደለም፡፡ኢየሱስ ዛሬ ይቅርታን ወይ ምህረትን እንድንቀበል የሚያስችለን አጋጣሚ ፈጠረልን፡፡
ኃጥአታችን እንዲሰረይልን ሁለት ነገር ማድረግ አለብን፡
እግዝአብሔር ይቅር ስለን ኢየሱስ ስለሞተልን ኃጥአታችን ድጋሜ አይቆጥርብንም፡፡ እርሱ ልንቀጣበት የነበረውን የኃጥአታችንን ዋጋ ተቀበለ፤ እኛም ነጻ ወጣን፡፡ በዚህ እውነት መሰረት፣ እኛ በደለኞች ሆነን ሳለን እግዝአብሔር መልሰው በበደላችን አይቀጣንም፡፡ አመጸኞች ሆነን ሳለን ቅዱሰን አደረግን፡፡ ይህ ከእግዝአብሔር ጋር ለመታረቅ መሰረት ነው፡፡ ምንኛ መታደል ነው!
እኛ ለበደሉን ሰዎች ይቅርታ ስናደርግላቸው የተደረገውን ነገር እንረሰዋለን ወይም እንክዳለን ወይም እንደመስሳለን ማለት አይደለም፡፡ በዚህ አውድ፣ “ይቅርታ ማድረግ” ማለት ማተው ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ለእግዝአብሔር አሳልፈን መስጠት አለብን፡፡ እንድን ሰው ይቅር ስንል፣ ሁሉንም ነገር ለእግዝአብሔር ትተን ማለት ነው፣ ከሰውዬው ጋር ያለን ሕብረት ከኃጥአት ሸክም ነጻ ይሆናል፡፡ በጭራሽ ቂም መያዝ ወ ይ መበቀል ማሰብ የለብንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ከሸክም ነጻ ወጥተን ከርሱ ጋር እንግባባለን፤ በደል ከዚህ በኋላ በመካከላችን አይኖረናል፡፡
![]() |
![]() |
![]() |