አካፍል
- በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋራ እንዴት ሳለፍክ/ሽ?
- እንድታመሰግን ያደረገ ነገር ምንድር ነው?
- እግዝአብሔር ምን እንዲረዳህ ትፈልግሃለህ?
- በምያስፈልግህ ነገር ውሰጥ እንዴት ልንረዳህ እንችላለን;
- ለእርስበርሳቸችሁ ፀልዩ
ክለሳ
- ከባለፈው ስብሰባችን ወዲህ ምን ምን ተለማምደሃል?
- እያንከባከብካቸው ያሉተ ሰዎች እንዴት ናቸው? በጣም የሚጠቅማቸው ነገር ምነድር ነው?
- የእግዝአብሔርን ለሌሎች ማካፍል ትችላለህ? ከነርሱ ጋር ፀልየሃል?
- ለነዚያ ሰዎች ፀልይ
የኢየሱስ ፊልም
የኢየሱስ ፊልም ተመልከት (እዚህ ይገኛል )
ይህ የኢያሱስን ሕይወት፣ አስተምህሮ እና በትክክል ይገልፃል፡፡ ይህን ፊልም በሦስት መንገድ ለማየት መወሰን እንችላለን፡
- እንደ ታሪክ ፊልም፡ በዚህ እይታ በፊልሙ የሚታየው ነገር ሁሉ ከ2000 ዓመት በፊት የተፈመ ታሪክ ብቻ ይሆንብናል፡፡ እንዲሁም አሁን ላይ ምንም ጥቅም እንደሌለ መቁጠራችን፡፡
- እንደ የሰው ድህነት፡ በዚህ አቋም ፊልሙን የምታይ ከሆነ፣ ኢየሱስ ለመላው ሰው ልጅ ኃጥአት ሞተ፤ እኔን ግን ከቢሊዮኖች አንድ ስለሂንኩኝ ብዙም አይመለከተኝም ማለትህ ነው፡፡
- እንደ የራሴ መዳኛ: ፊልሙን በዚህ እዪታ፣ ኢየሱስ ለእኔ ሲል ተሰቃየ ብለህ፣ በእውነት ምን እንደ ተፈጸመ ትረዳለህ፡፡ ይህ ፊልም ስለ እኛ መሆኑን ደጋግመን ራሳችን ማሳመን አለብን፡፡ አንድ ሰው ስለ እኔ ተጨነቀ፣ ብዙ ስቃይንም ተቀበለ፤ ይህ ሁሉ ከክፋት ነጻ አውጥቶኝ ከእግዝአብሔር ጋር ደጋሜ አገናኘኝ ብለን ማመን ነው፡፡
ከቪዲዮው ምን ያህል አብራችሁ ለማየት ወስኑ፡፡ ሙሉ ፊልሙን ለማየት ግዜ ከሌለህ፣ አንድ ሰዓት ላይ ምልክት አርገህ ተመልከት፡፡ ይህ የኢየሱስ ወደ እየሩሳሌም ገብቶ ተሰቃይተው ከመሞቱ በፊት የተናገራቸው ምሳሌዎች፣ ትምህርቶች እና ታመራት እንድታገኝ ይረዳሃል፡፡
1:15 ላይ አቁም
- ኢየሱስ ከተናገራቸው ወይም ከሰራቸው ልብህን የነካ ምንድር ነው?
- ኢየሱስ ተልዕኮውን ወይም አላማውን እንዴት ነበር የገለጸው? (see 1:14)
- ኢየሱስ እርሱ ላይ ምን ልፈጸም እንዳለ ነው የተናገረው? (1:15)
1:43 ላይ አቁም
- ጲላጦስ ስለ ኢየሱስ የነበረው አመለካከት ምን ነበር?
- ጲላጦስ ኢየሱስን ለምን ነበር የቀጣው?
ከፊልሙ በኋላ
- ኢየሱሰ ለኔ ሲል እንደዚህ መሰቃየቱ ምንድር ነው?
ተግዳሮት
- እምነትህን በእየሱስ ላይ ዛሬ ለማድረግ ትፈልጋለህ?
- ከጌታ ጋር ያለኝን ልምዴን ለሆነ ሰው ለማካፈል እና ከጌታ ጋር ህብረት እንዲኖረው ለመጋበዝ በሚቀጥለው ሳምንት እድሉን የማገኘው የት ነው