ትንቢተ ኤርምያስ 31:31-34
31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤
32 ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
34 እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።
ትንቢተ ኢሳይያስ 59:1-2
1 እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፥ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም፤
2 ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
ታማኝ እንሁን፡፡ አስርቱን ትዕዛዛት በትክክል እየጠበቅክ ነው ወይስ በተከታታይ እየጣስካቸው መሆኑ ተሰምቶሃል? እነኚህ ሕጎች ክፋትን ለመከላከል ብጠቅሙም፣ ጨርሰው ልደመስሱ አይችሉም፡፡ እኛ ሰዎች ክፋት ነጻ መሆን እራሳችንም መቀየርም የማንችል መሆኑ የማይቀየር እውነት፡፡
ለዚህ ነበር እግዝአብሔር ልመጣ ስላለው የአዲስ የህይወት መንገድ ዘመን የተናገር ነው፡፡ ይህ ልሆን ዘንድ መቀየር ያለበት ነገሮች አሉ፡
![]() |
![]() |
![]() |