4.

አስር ነገሮች

አካፍል
  1. በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋራ እንዴት ሳለፍክ/ሽ?
  2. እንድታመሰግን ያደረገ ነገር ምንድር ነው?
  3. እግዝአብሔር ምን እንዲረዳህ ትፈልግሃለህ?
  4. በምያስፈልግህ ነገር ውሰጥ እንዴት ልንረዳህ እንችላለን;
  5. ለእርስበርሳቸችሁ ፀልዩ
ክለሳ
  1. ከባለፈው ስብሰባችን ወዲህ ምን ምን ተለማምደሃል?
  2. እያንከባከብካቸው ያሉተ ሰዎች እንዴት ናቸው? በጣም የሚጠቅማቸው ነገር ምነድር ነው?
  3. የእግዝአብሔርን ለሌሎች ማካፍል ትችላለህ? ከነርሱ ጋር ፀልየሃል?
  4. ለነዚያ ሰዎች ፀልይ
አንብብ
  1. ንባቡን ድምጽህን ከፍ አርግና ሁለት ግዜ አንብብ
  2. በቡድኑ እርዳታ አንድ ሰው ንባቡን በቃሉ እንዲያነብ አርጉት
  3. የተጨመረ አዲስ ነገር ወይም የጎደለ ነገር አለ?

ኦሪት ዘዳግም 5:6-22

6 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።

7 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።

8 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤

11 የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።

12 እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ ጠብቅ።

13 ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፥

14 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር አምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ ሎሌህና ገረድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም ሎሌህም ገረድህም በሬህም አህያህም ከብትህም ሁሉ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ።

15 አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ የሰንበትን ቀን ትጠብቅ ዘንድ አዘዘህ።

16 እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ።

17 አትግደል።

18 አታመንዝር።

19 አትስረቅ።

20 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።

21 የባልጀራህን ሚስት አትመኝ፤ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።

22 እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመናው በጨለማውም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ተናገረ፤ ምንም ምን አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጣቸው።


በስፋት አንብብ

አጣራ
  1. ይህ ንባብ ላንተ ምን ጥቅም አለው?
  2. ከዚህ ንባብ የወደድከው ነገር ወይ የረበሸ ነገር አለ?
  3. የህ ንባብ ስለ ሰው እና ስለ እግዝአብሔር ምን ይነግርሃል?
አተግብር
  1. የህን ንባብ መሰረት በማድረግ ታደርግ ዘንድ እግዝአብሔር ካንተ የሚፈልገውን ነገር ጠይቅ፤ ምን ምን ናቸው?
    • መቀየር ያለበት ፀባይ
    • መጠየቅ ያለበት ቃል ክዳን
    • መከተል የሚገባው ምሳሌ
    • መጠበቅ ያለበት ትዕዛዝ
  2. ይህን ለቡድኑ አካፍል
ማስታወሻ

ራስ ወዳድነት እና ክፋት ከቁጥጥር ወጥተው እንዳይስፋፋ ከውሃ ጥፋት በፊትም እግዝአብሔር ገደብ አድርገውበት ነበር፡፡ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ሕጎች “ስርቱ ትዕዛዛት” ይባላሉ፡፡ እነኚህ ሕጎች ተቀባየነት ያለውንና የሌለውን ባህርይ ለመለየት የስችሉናል፡፡ ስህተትን ለመቅጣት፣ ክፋት እንዳያስፋፋ እና የሰውን ዘር እንዳያበላሽ ለመከልከል መሰረት ናቸው፡፡ ከእግዝአብሔር ጋር (የመጀመሪያ አምስቶቹ) እና ከእርስበርሳችን (የሁለተኛውን ምስቶች) የነበረን ሕብረት እንደ ፈረሰ ገልጦ ይነግረናል፡፡