1.

ገነት

አካፍል
  1. በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋራ እንዴት ሳለፍክ/ሽ?
  2. እንድታመሰግን ያደረገ ነገር ምንድር ነው?
  3. እግዝአብሔር ምን እንዲረዳህ ትፈልግሃለህ?
  4. በምያስፈልግህ ነገር ውሰጥ እንዴት ልንረዳህ እንችላለን;
  5. ለእርስበርሳቸችሁ ፀልዩ
ክለሳ
  1. ከባለፈው ስብሰባችን ወዲህ ምን ምን ተለማምደሃል?
  2. እያንከባከብካቸው ያሉተ ሰዎች እንዴት ናቸው? በጣም የሚጠቅማቸው ነገር ምነድር ነው?
  3. የእግዝአብሔርን ለሌሎች ማካፍል ትችላለህ? ከነርሱ ጋር ፀልየሃል?
  4. ለነዚያ ሰዎች ፀልይ
አንብብ
  1. ንባቡን ድምጽህን ከፍ አርግና ሁለት ግዜ አንብብ
  2. በቡድኑ እርዳታ አንድ ሰው ንባቡን በቃሉ እንዲያነብ አርጉት
  3. የተጨመረ አዲስ ነገር ወይም የጎደለ ነገር አለ?

ኦሪት ዘፍጥረት 2:4-25

4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።

5 የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም ነበር፣ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤

6 ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር።

7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

8 እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።

9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

10 ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር።

11 የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤

12 ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል።

13 የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።

14 የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው።

15 አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።

16 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤

17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።

18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።

19 እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ።

20 አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።

21 እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው።

22 እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።

23 አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።

24 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።


በስፋት አንብብ

አጣራ
  1. ይህ ንባብ ላንተ ምን ጥቅም አለው?
  2. ከዚህ ንባብ የወደድከው ነገር ወይ የረበሸ ነገር አለ?
  3. የህ ንባብ ስለ ሰው እና ስለ እግዝአብሔር ምን ይነግርሃል?
አተግብር
  1. የህን ንባብ መሰረት በማድረግ ታደርግ ዘንድ እግዝአብሔር ካንተ የሚፈልገውን ነገር ጠይቅ፤ ምን ምን ናቸው?
    • መቀየር ያለበት ፀባይ
    • መጠየቅ ያለበት ቃል ክዳን
    • መከተል የሚገባው ምሳሌ
    • መጠበቅ ያለበት ትዕዛዝ
  2. ይህን ለቡድኑ አካፍል
ማስታወሻ

ሰማይ፣ ምድር፣ ሰዎች፣ እንስሳት እና እፅዋት የተገኙት እንደ አጋጣሚ አይደለም፡፡ ሁሉም በእግዝአብሔር ተፈጠሩ፡፡ ከመጀመሪያ ጀምሮ ሰዎች እርስበርሳቸውን እና የሚኖሩበትን አለም እንዲጠብቁ ትልቅ ኃላፍነት ተሰጣቸው፡፡ ሁሉም ነገሮች የእግዝአብሔርን መልካምነት ያንጸባርቃሉ፡፡ ወንድ እና ሴት በተፈጥሮ እንዲደሰቱ ነጻነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ እግዝአብሔርን የመታዘዝና የለመታዘዝ፣ ፍቅሩን የመቀበል እና ያለመቀበል ነጻነት እንኳን ተሰጥቷቸዋል፡፡ በሁለቱም መካከል የነበረው መተማመን ትልቅ ነበር፤ ራቁት ብሆኑም አይተፋፈሩም፣ እርስበርሳቸውም ለመደባበቅ ልብስም አልፈለጉም ነበር፡፡

የምገርመው፣ ሰው መልካምን እና ክፉን የምታሳውቅ ፍሬ በመብላት እግዝአብሔርን ያለመታዘዝ አማራጭም ተሰቷቸው ነበር፡፡ ግን የዚህ ጥፋት ቅጣት ሞት እንደሆነ አስጠንቅቋቸውን ነበር፡፡ የዚህ ተክል መገኘት ሰዎች ሙሉ በሙሉ በእግዝአብሔር ፍቃድ ምህረት አለመሆናቸውን ያሳያል፡፡የሰው ልጅ የምርጫ ነጻነት አለው፡፡ የእግዝአብሔርን ፍቅር የመቀበል እና የመተው ነጻነት ተሰጥተው ነበር፡፡